Mahmoud Mohammed Interview
Audio File:
Download File: Download Transcript:
Open/Close
ይህ ቦታ አሊ ወዮ ይባላል
እኔ ፕሮፌሰር ጌትነት በቀለ ነኝ
አቶ መሀመድ አህመድ ጋር የተደረገ ጥያቄና መልስ ነው
July 31
ጥ. ሞዴል ገበሬ ነህ ተብሏል እንዴት ተመረጥክ ?
መ. ለመጀመሪያ ጊዜ ህይወቴን ለማሻሻል በማደርገው ጥረት ወደግብርና ገብቼ ሥሠራ ኑሮዬን ለማሻሻል በምጥርበት ወቅት ጥሩ ገበሬ ነህ ትብዬ እረዱኝ እኔም በእርዳታው ራሴን እያሻሻልኩ ሄድኩኝ
ጥ. ስንት ዓመት የሆንሀል እራስህን ችለህ ግብርና ስትሠራ ?
መ. አሁን 15 ዓመት ይሆነኛል
ጥ. መሬት እንዴት አገኘህ ?
መ. ከቤተሰብ ነው ያገኘሁት እንጂ ከቀበሌ ምንም አላገኘሁም
ጥ. አባትህ እዚህ ቅርብ አሉ የትኛው ነው የሳቸው መሬት ?
መ. የሳቸው መሬት ራቅ ይላል አነስተኛ ነው
ጥ. ይሄ መሬት ታዲያ የማን ነው ?
መ. እዚህ የቀበሌ ወፍጮ ቤት ነበር እሱን ስጠብቅ ነው የሰጡኝ
ጥ. ስንት ነው ታዲያ ይሄ ስፋቱ ?
መ. ያኔ ሲሰጡኝ እንኳን ትንሽ ነው አሁን 2 ጥማድ ይሆናል
ጥ. አንድ ጥማድ ስንት ነው በሄክታር ?
መ. ግማሽ ሄክታር ማለት ነው
ጥ. በዚህ 15 ዓመት ውስጥ ምንድነው በብዛት የምታመርተው በማሳህ ላይ
መ. ማሳ ላይ በቆሎ፣ ስንዴ አንዳንዴም ሽንኩርት አመርታለሁ እዚህ ላይ ደግሞ የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ጥራጥሬ ነው የማመርተው
ጥ. ማሳህ ስንት ሄክታር ይሆናል ?
መ. አንድ ሄክታር ይሆናል
ጥ. እዛ ቤት አለህ ማን ይጠብቅልሀል
መ. ሁሉም እኩል ስለሚዘራ ከብት ስለማይለቀቅ ጠባቂ አያስፈልገውም
ጥ. ወተር ፖምኘ አለህ አሉ እውነት ነው ?
መ. አዎ አለኝ
ጥ. በአሁኑ ወቅት ያለው የገበሬ ችግር ምንድን ነው አንድ ሰው መጥቶ አንድ ችግርህን ልፍታልህ ቢልህ ምን ትላለህ ምንድነው የምትመርጠው ?
መ. እኔ በበኩሌ የገበሬዎች ገበሬነት ቢሰማን ጥሩ ነው የዚህ ኩሬ ሸራ ብቻ ነው ሌላው በሙሉ እራሴ መስራትና ማግኘት እችላለሁ በግዢም ይከብዳል አሉ አሁን የሚመጡ ድርጀቶች እርዳታ ይሰጣሉ ይባላል፡፡ የማመርተው በዚህ ኩሪ ስለሆነ ውሃው እንዳይሰምጥ ሸራ እፈልጋለሁ ችግሬ ይሄ ነው፡፡
ጥ. ማዳበሪያ ትጠቀማለህ ?
መ. እዚህ ግቢ ውስጥ አልጠቀምም በኮምፖስ ነው የምጠቀመው ማሳ ላይ ግን እጠቀማለሁ
ጥ. የማዳበሪያ ዋጋ እንዴት ነው ከአቅም በላይ ነው ወይስ ይቻላል ?
መ. የማዳበሪያ ጉዳይ ብዙ ውጣ ውረድ አለው በእህሉ ዋጋ ደረጃ ስታየው ውድነው ባይባልም ግን ዋጋው ከፍ ዝቅ እያለ ገበሬው የሚበዘበዝበት ሁኔታ አለ ገበሬው ለሽያጭ በሚያቀርብበት ጊዜ ነጋዴው ዝቅ ያደርግና ገበሬውም ዕዳውን ለመክፈል ሽጦ ይከስራ፡፡ ግን በገበሬ አያያዝ አቆይቶ መሸጥ ስለማይችል ኪሳራ ይገባል ከዚህ ሁኔታ ሲታይ እንጂ ውድነው አይባልም ገበሬው በወቅቱ ማስቀመጥ ስለማይችል ነው፡፡
ጥ. ከዚህ ከኩሬ ጋር ተያይዞ የወባ ስጋት አለ ምክንያቱም ትንኞች እንደዚህ ዓይነት ውሃ ካገኙ በቀላሉ ይራባሉ ይህ እንዳይሆን መምድነው የምታደርገው
መ. እኔ በግሌ የምጠቀመው ለዚህ ኩሬ ስጋት ስላለኝ ከብትም እዚህጋ ስለሚያድር በሳምንት አንድ ጊዜ መድሀኒት እረጫለሁ ማታ ማታ ፋኖስ አበራና በብዛት እሱ ላይ ሲሰበሰቡ መድሀኒት እረጫለሁ፡፡ አንዳንዴም ሳምንትም ላልቆይ እችላለሁ እስካሁን ያጋጠመኝ ችግር የለም
ጥ. ማላታይን ነው የምትረጨው ?
መ. አይ እኔ በግሌ ነው የግል ተሞክሮ ነው መንግስት የወባ መከላከያ አጎበር ይሰጣል ዲዲቲም ይረጫል፡፡ አንዳንድ አካባቢዎች በጣም የጎላ የወባ ችግር አለ እዚህም አካባቢ በፊት ነበር አሁን ግን አቅሟ ደክሟል የለም ነው የሚባለው፡፡
አመሰግናለሁ፡፡
1
Courtesy of Getnet Bekele
Creator: Mohammed, Mahmoud
Bekele, Getnet
Contributing Institutions: Getnet Bekele, MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University
Description:
-
His own experience as a “model farmer.”
-
Remarks on the challenges he and most farmers now face in agriculture.
-
Comments on water resources and hiking fertilizer prices.
-
Malaria prevention.
-
Interview conduced in Ali Wayao, just to the north of Arsi Nagelle town, Lake region, Ethiopia
Date: July 31, 2010
Location: Ali Wayao, Ethiopia
Format: Audio/mp3
Language: Amharic
Rights Management: For educational use only.
Digitizer: MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University