Nini Abino Interview
Audio File:
Download File: Download
Download File: Download
Transcript:
Open/Close
ከጋሽ ኒኒ ጋር ተገናኝተን ስለ አርሲ ነገሌ እየተነጋገርን ነው ዛኔ ቀኑ ነሀሴ 7/2ዐዐ1 ዓ.ም. ነው፡፡
ይሄ የማሳይህ ወረቀት የግማጅ እቴጌ ግዛት ውስጥ የወረዳ ግዛት ያለ የመሬት ግዛትና ክፍፍል ሰንጠረዥ ነው፡፡
ጥ. እኚህ ሰው ብዙ እንደዚህዓይነት ወረቀት ይኖራቸው ይሆን እኔ ፎቶ ኮፒ አድርጌ ብወስድ
መ. እኔ ይሄ ስለሚያስፈልገኝ ነው የወሰድኩት ሊኖር ይችላል ማረጋገጥ እንችላለን፡፡
ጥ. አንዳንድ መረጃዎች ያለታሰበ ቦታ ይገኛሉ ካለና የሚገኝ ከሆነ ይጠይቁልኛል
መ. እናጣራለን፡፡ በነገሌ ወረዳ 7 ባላባቶች ይገኛሉ እነርሱም እነሙራ፣ ኒኒ ፣ ማለዳ፣ዋጂ ዳዬ፣ እኛምሜ እሄቶታ ናቸው የመሬት ክፍፍሉም፡-
• የግማጅ እቴጌ ጋሻ 659 ተኩል
• የገባር ባለርስት 479
• የሰሞን 67ጋሻ
• የባላባት መጦሪያ 73 ጋሻ
• ስመጥሩ የኤርትራ ወያን 191.25 በድምሩ በወረዳው 1469.75 ጋሻ መሬት ነበር
ጥ. በጠቅላላው የነገሌ ጋሻ ርስት ስንት ይሆናል?
መ. 1469.75 ነው ከላይ የዘረዘርኩት በሙሉ እሱ ነው
ጥ. እነዚህ ባላባቶች በቱኬ ጊዜ የተሾሙ ናቸው?
መ. ቱኬ እኮ አገር ገዢ ነበሩ አርሲን ከብላቴ ወንዝ ጀምሮ እስከ ዋዜ ድንጋይ ይገዙ ነበር
ጥ. እነሾኒንም በእርሱ ስር ነው ያሉት?
መ. ሾኒ አይሻገርም ሾኒ የሚገዛው ሀዲያ በጢሶ በላ ነው እርሱ ሀዲያና አላባን ይገዛል
ጥ. ሾኒ ኦሮሞ አይደለም እንዴ?
መ. ሾኒ ሀድያ ነው አፄ ምኒልክ በዘዴ ነው ያስቀመጡት ወላይታ በጦና ጋጋ ሀዲያ በገዲሳ በላ እነዚህ ባላባቶች ከ1923 ጀምሮ ነው የነበሩት
ጥ. ምን ያህለ ጋሻ ይገዛ ነበር ቱኬ ማማ ይህን ያክላል?
መ. ከዚህ ይበልጣል ከዋንዛበል እስከ ዋቤ በሰሜን እስከ አዋሽ ያለውን ነበር የሚገዛው
ጥ. በሻሸመኔ በኩል አድርገን አላባ ሄደን ከዛ የሻላን ሀይቅ አየነው እዛ ያሉት ሕዝቦች እነማናቸው?
መ. አላባዎችም ኦሮሞዎችም አሉ
ጥ. እነርሱ የምን ኦሮሞ ናቸው የአርሲ ወይስ የሊበን?
መ. የአርሲ ኦሮሞ ናቸው
ጥ. ቱኬ ማማ እነዚህ ሁሉ ያስተዳድር ነበር?
መ. አዎ ቱኬ መንግስትን እንዲጋራ ነበር በአርሲ አባ ገዳ የተሾመው
ጥ. ማን ነበር የአርሲ አባገዳ?
መ. ጂኖ ሮባ ይባላል ቱኬን የወከለው
ጥ. ቱኬ በዛን ወቅት ወጣት ነበር ማለት ነው?
መ. አዎ ወጣት ነው
ጥ. ጂኖ ሮባ ጎሳው ምን ነበር ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ነው?
መ. ኢቤኖ ነው እነዚህን ሰዎች ለሹመት የሚያመጣው አባ ገዳ ነው ድሮ በምኒልክ ጊዜ በጎሳ እንዲስፋፋ የሚያደርገው አባ ገዳ ነው እንደመንግስት ድሮ አባ ገዳ እምነት ይጣልበታል
ጥ. በድሮ ጊዜ አባገዳ ከኤቢኖ ጎሳ ብቻ ነው የሚመረጠው?
መ. አባ ገዳ የሚመረጠው ከአንጋፋ ነው ሁሉም ጎሳ አባገዳ አለው ጠቅልሎ የሚይዘው ግን ኤቢኖ ነው የአርሲ ልጆች የመጀመሪያ ታላቅ እርሱ ነው፡፡
ጥ. በአርሲ ነገሌ ጎሳዎች መካከል አንዱ ኤቢኖ ነው ሌሎቹ እንማን ናቸው?
መ. ከስምንት በላይ ጎሳዎች አሉ ኤቢኖ ታላቅ ነው ኤቢኖ መሬትም የለውም ሀብትም የለውም እሱ መሬት እንዳያገኝ የሚያደርገው የአባ ገዳ ህግ ነው እርሱ ታላቅ ስለሆነ ሁሉም የእርሱ ነው፡፡
ጥ. ኤቢኖ ከግብር ነው ጥቅም የሚያገኝ ወይስ ከምን ነው?
መ. ምንም ግብር የለም በዓመት በዓል በሚከበርት ወቅት ሁሉም የሚያስፈልገው ያስገባሉ፡፡
ጥ. የያንዳንዱ ጎሳ አባ ገዳ ግን የጎሳው መሬት ባለቤት ነው ሀብቱ የእርሱ ነው?
መ. የመሬት ባለቤትነት አሁን በአፄ ሀ/ስላሴ ነው የመጣው ድሮ ይሄ ጋሻ የዚህ ነው የሚል የለም
በቱኬ ማማ ጊዜ ግብር የሚገበረው በመሬት ብዛት ነው አንድ መሬት ካለ አንድ ብር ነው ስፋት አይታይም
ጥ. ባላባቶቹ የመሬት ባለቤት የሆኑት በአፄ ሀ/ስላሴ ጊዜ ነው ማለት ነው?
መ. አዎ
ጥ. በድሮ ጊዜ ሰው የሚበላው ማርና ገንፎ ነው ብላችኋል ገንፎው የምንድን ነው?
መ. የገብስ
ጥ. ገብሱ ከየት ይመጣል?
መ. ገብስ ድሮም አለ በኦሮሞ ውስጥ የሚዘራው ትልቁ እህል ገብስ ነው ገብስና ቡና ባያርሱም በልውውጥ ያመጣሉ ለአምልኮ ሲሰበሰቡም ገብስና ቡና አይጠፋም
ጥ. ከአድዋ በፊት ነው ጎበና ይህንን አካባቢ ያስከበሩት ብለውኛል በግምት ከአድዋ 1ዐ ዓመት በፊት ይሆናል?
መ. ይህን ያህል ለይቼ ባላውቅም በአድዋ ያልኩበት በአድዋ ዘመቻ ከዚህ አካባቢ ሄደው የተዋጉ አሉ የኛ አባት ትልቅ ወንድምም ሄደው ተዋግተዋል ተርፈው መጥተው አዲስ አበባ ነበሩ
ጥ. ማን ይባላሉ?
መ. ከዚህ ሲሄዱ ጎበና ጂዶ ተዋግተው አዲስ አበባ ሲገቡ ተሰማ ጎበና ተብለዋል፡፡
ጥ. ስለዚህ በዚህ ሲገመት ቢያንስ ቢያንስ ከዛ በፊት ትንሽ ጊዜ አለው ማለት ነው?
መ. ብዙ ባላባቶች አሉ ታዋቂ ሰዎችም የዘመቱ አሉ ስለዚህ ነው ከዛ በፊት የተባለው?
ጥ. ያኔ ሲነግሩኝ ካስገበሩ በኋላ ጎበና ቱኬ ማማን መሬት ስጠኝ ብለው ጠየቁና መሬት ሰጣቸው ብለውኝ ነበር ቁጥሩ ይታወቃል ምን ያህል ለመንግስት ምን ያህል ለባላባት እንደቀረ?
መ. አሁን እኔ የማላውቀው ቱኬ ማማ ለመንግስት የሰጠው መሬት ምን ያህል እንደሆነ ነው ግን በዛ ወቅት መሬቱ በጋሻ የታወቀ አይደለም
ጥ. ጣሊያን አሩሲ ነገሌ መጥቶ ነበር እርሻ ጣሊያን የጀመረ ይመስሎታል?
መ. ጣሊያን እርሻ አልጀመረም
ጥ. ምንም ነገር?
መ. ምንም እርሻ አልጀመረም በጦርነት ላይ ነበር ነገሌ ከማለፍ በስተቀር ብዙም አላረፈበትም ሻሸመኔ ነው
ጥ. ቤተርስት ብለው አፄ ኃ/ስላሴ ሲመሰርቱ ከመሬት ተነስተው ነው እንጂ ምንም ነገር አልነበረም?
መ. አዎ ምንም አልነበረም
ጥ. ቤተርስት ስንዴ ለማምረት ነው የተጠቀሙበት ማለት ነው ?
መ. አዎ ቤተርስት ስንዴ ለማምረት ብቻ ነው የተጠቀሙበት
ጥ. ቤተርስት ጣሊያን እንደወጣ አይደለም የተመሠረተው ቆይቶ ነው ማለት ነው?
መ. ቤተርስት የተመሠረተው አፄ ሀ/ስላሴ በ1923 ስልጣን ላይ ወጡ መሬት እየከለሉ እያሉ ጦርነት ተነሳ መልሰው ሲያሸንፉ በ1937 ጋሻው ተለካ በድጋሚ በ1942 እንደገና በተሻሻለ ሁኔታ በመረሻም በ1952 ነው
ጥ. እስኪ ስለወረገኑ ይንገሩኝ መቼ ቀረ?
መ. በትክክል ወረገኑ የሚባል ነገር የለም
1

Transcript: Download (189 KB)
Courtesy of Getnet Bekele
Creator: Abino, Nini
Bekele, Getnet
Bekele, Getnet
Contributing Institutions: Getnet Bekele, MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University
Description:
- History of local society
- History of land tenure
- History of local administration
Date: August 15, 2010
Location: Arsi Nagalle, Ethiopia
Format: Audio/mp3
Language: Amharic
Rights Management: For educational use only.
Digitizer: MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University